Wendi Mak / ወንዲ ማክ - Bibal / ቢባል - Ethiopian Music 2023(Official Video)
✔️ Click Here for More
Musics
Wendi Mak / ወንዲ ማክ - Bibal / ቢባል - Ethiopian Music 2022(Official Video)
Any unauthorized use, copying or distribution is strictly prohibited By Wendi Mak.
Copyright ©2023: Wendi Mak .
#Bibal #wendimak #ethiopianmusic #ቢባል
------------------------------------------------------
መቆም ነው መገለጥ መኖርሽ ለኔ አለም
መፍካትና ማበብ መድመቅ ነው መቀለም
ሁሌ ሙሽራ ነኝ የስክነት ተራማጅ
ሁልግዜ ንግስናን ቆጥሮ ተለማማጅ
ብዬም አስባለሁ እስኪ ምን ልበላት
በምን ቃል አጊጬ በምን ልሞሽራት
ቃላት ሰካክቼ ያልደረስኩት እውቀት
እሷ እንዲህ ናት ብሎ በአንድ ቃል ማሰንበት
ብዬ ብዬ እንዲያ እንዲህ ናት ብዬ
ብዬ ብዬ እሷ እንዲህ ናት ብዬ
አንደበቴ ሊገልፅሽ ይልና
ቃላት ያጣል ደግሞ እንደገና
ቢባል ቢወራ ስላንቺ አይሰለች
እኔን ሰርተሽ አበቃሽኝ ሰው አረግሽኝ (×2)
🎶🎶🎶🎶
አንደበቴ ሊገልፅሽ ይልና
ቃላት ያጣል ደግሞ እንደገና(×2)
ልዑል አልጋ ወራሽ ራስ ፊትአውራሪ
ግራአዝማች ቀኝአዝማች ለጌታው አዳሪ
ስሜቴ እንደሱ አይደል እንደንጉስ ብቻ
የምናቡ ዘውዴ በየትኛው ክተት ነው በየትኛው ዘመቻ
ቢባል ቢወራ ስላንቺ አይሰለች
እኔን ሰርተሽ አበቃሽኝ ሰው አረግሽኝ
🎶🎶🎶🎶
የአይኔ ቀለም ከአይንሽ የመመሳሰሉ
ተፈጥሮ አቆንጅቶ አስውቦን መኳሉ
የገነትን ግርዶሽ የመግፈፍ ተምሳሌት
እንዲያ ይሰማኛል አብሬሽ ከአንቺ ጋር ቀን ከሌት
🎶🎶🎶🎶
ሀይል እውቀት ለእኔ ሰውነት
ፍቅር ስክነት ለእኔ ሰውነት
ዘርተሽ በቅሎ አሁኔን መስሎ
ፅናት ሰጥቶሽ ሁሉን አስችሎሽ
ቢባል ቢወራ ስላንቺ አይሰለች
እኔን ሰርተሽ አበቃሽኝ ሰው አረግሽኝ(×2)
🎶🎶🎶🎶
ግጥምና ዜማ -
ወንዲ ማክ (ወንወሰን መኮንን)
----------------------------------------------------------
Show more
