Playing Next....


      ደጌ | Dege by Sami-Dan



      ✔️ Click Here for More Musics

      New Ethiopian Music 2018/2025

      ደጌ

      ሆ ግዶ
      ደጌ...

      ደጌ ደጌ ጉራጌ
      ደግ ነው ደጌ ጉራጌ

      በጠዋት ተነስቶ ስራው ላይ ሚለፋው
      ሀገር እንዳቀና ይናገራል ትከሻው
      ከሰው የማይደርሰው ለሰው ግን ሚተርፈው
      የአባቶች ምርቃት ጉልበት እየሆነው

      ለተሻለ ኑሮ ቢወጣም ካገሩ
      ሀገር ቤት ነው ልቡ ካደገበት መንደሩ
      የተንቢ እያለ ይመጣል መስቀል ላይ
      የናፈቀችውን እናቱን አይኗን ሊያይ

      ሆ ግዶ

      በኔና - ጉራጌ
      በፍቂር - ጉራጌ
      በንማጀ - ጉራጌ
      ድረምንቅ - ጉራጌ

      ጉራጌ አቤት ሲያምርበት
      ጭፈራውን ሲችልበት
      ባንድነት ሆኖ ሲያከብር
      ይነግሳል በቤቱ ፍቅር

      አባኸ - ሽማኸ
      እማኸ - ሴራኸ
      ጥብጥና - ምሽራኸ
      ሙረኽ - ጥባኸ

      ደጌ ጉራጌ

      የሴቶቹ መስቀል ላይ ደርሼ
      የጎመኑን ክትፎ ቀምሼ
      እንዴትስ አድርጋ ብትሰራው ነው
      ስበላው አንጀቴን የሚያርሰው
      ሆ ጉራጌ ናትና ውቢቷ
      ወርሳዋለች ሙያውን ከናቷ
      በሰራችው ጅባ ላይ ተኝቼ
      አልሄድም ከቤቷማ ወጥቼ
      የደመራው መብራት ፊቴ ላይ
      አበራው ተስፋዬን አውጥቶ እንደ ፀሀይ
      ያባቶች ምርቃት ፍቅራቸው ሲደርሰን
      ስንጨፍር ባንድ ላይ ደመራውን ከበን
      ኬር ይሁን ይላል ላገሩ ሲማፀን
      አሚን አሚን አልን በተስፋ ተውጠን
      ያርግለት የልቡን ከተመኘውማ
      ፈጣሪም ይራራል ይሄንን ሲሰማ

      ደጌ ጉራጌ

      ደጌ ደጌ ጉራጌ
      ደግ ነው ደጌ ጉራጌ

      በጠዋት ተነስቶ ስራው ላይ ሚለፋው
      ሀገር እንዳቀና ይናገራል ትከሻው
      ከሰው የማይደርሰው ለሰው ግን ሚተርፈው
      የአባቶች ምርቃት ጉልበት እየሆነው

      ለተሻለ ኑሮ ቢወጣም ካገሩ
      ሀገር ቤት ነው ልቡ ካደገበት መንደሩ
      የተንቢ እያለ ይመጣል መስቀል ላይ
      የናፈቀችውን እናቱን አይኗን ሊያይ

      ሆ ግዶ

      በኔና - ጉራጌ
      በፍቂር - ጉራጌ
      በንማጀ - ጉራጌ
      ድረምንቅ - ጉራጌ

      ጉራጌ አቤት ሲያምርበት
      ጭፈራውን ሲችልበት
      ባንድነት ሆኖ ሲያከብር
      ይነግሳል በቤቱ ፍቅር

      አባኸ - ሽማኸ
      እማኸ - ሴራኸ
      ጥብጥና - ምሽራኸ
      ሙረኽ - ጥባኸ

      ደጌ ጉራጌ

      ደጌ Credit

      Melody : - Sami-Dan
      ዜማ :- ሳሚ-ዳን

      Lyric :- Sami-Dan x Mewded Kibru
      ግጥም :- ሳሚ-ዳን እና መውደድ ክብሩ

      Arrangement :- Sami-Dan
      ቅንብር :- ሳሚ-ዳን

      Tenor Sax :- Ashenafi
      ቴነር ሳክሲፎን: - አሸናፊ

      Bass Guitar :- Jimmy ( Girma Moges )
      ቤዝ ጊታር :- ጂሚ ( ግርማ ሞገስ )

      Lead Guitar :- Robel Mehari
      ሊድ ጊታር :- ሮቤል መሀሪ

      Keyboard :- ጃሽ
      ኪቦርድ :- Josh

      Drum :- Addio (Addis Ras Band )
      ድራም :- አዲዮ ( አዲስ ራስ ባንድ )

      Mixing and Mastering :- Andy Bete Zema
      ሚክስንግና ማስተሪንግ :- ኤንዲ ቤተ ዜማ

      Background Vocal :- Esubalew Yitayew (Yeshi) | Henok Getachew , Kaleab Mulugeta | Shewalem Bade

      ተቀባይ ድምፅ :- እሱባለው ይታየው (የሺ) | ሔኖክ ጌታቸው | ቃለአብ ሙሉጌታ | ሸዋአለም ባዴ

      Show more

      Playing Next