Playing Next....


      ወስዳዋለች _ ሳሚ-ዳን / Wesdawalech _ Sami-Dan / New Ethiopian Music



      ✔️ Click Here for More Musics

      Song writer - Sami-Dan
      Arrangement - Flashkido
      Featuring - Kuul Sure
      Mastering - SoundBetter ( Matty LA )

      ወስዳዋለች

      ማነሽ ማነሽ
      ልቤን የወሰድሽ (2x)
      ህግ የለም ወይ ባገሩ ላይ
      ነይ እንጂ መልሽ
      በይ እንጂ መልሽ
      ነይ እንጂ መልሽ

      ሳላስበው በቆምኩበት
      ቀጥ የሚያረግ አየሁ ውበት
      ተገርሜ እኔ ስዘናጋ
      ልቤ ተሰርቆ ሄዷል እሷው ጋ
      አቅም የለኝ በምኔ ላውራት
      ልጅት ለኔ ጉዳይም የላት
      ደርቄ ቀረሁ ከመሀል ሜዳ
      ባይተዋር ነኝ ለፍቅር እንግዳ

      እግሬ እንዲሄድ ብለምነው አልሆንለት አለ
      በብዙ ሰው ተከብቤአለሁ ግን የሚረዳኝ የለ
      ህመሙ ሲበረታብኝ ደረቴን ብዳብሰው
      የለም ከኔ ምስኪኑ ልቤ ወስዳዋለች እች ሰው

      ኦ…..ወስዳዋለች

      ወስዳዋለች

      ማነሽ ማነሽ
      ልቤን የወሰድሽ (2x)
      ህግ የለም ወይ ባገሩ ላይ
      ነይ እንጂ መልሽ
      በይ እንጂ መልሽ
      ነይ እንጂ መልሽ

      በምታምነው ባምላኳ ስም
      ስለት ይግባ ለኔ ህመም
      ሽማግሌ ይፈለግና
      መላ ትባል ትገሰፅና
      በምናውቀው በህገ ልቦና
      የሰው ነገር የሰው ነውና
      ዳኛም ካለ ወይም ጠበቃ
      መልስ ትስጠኝ ያው ተጠይቃ

      ናፍቆቷ ውጋት እኮ ነው ሰቅዞ ይዞኛል
      ቀኑን ሙሉ አስባታለሁ ሌላማ መች ያምረኛል
      ህመሙ ሲበረታብኝ ደረቴን ብዳብሰው
      የለም ከኔ ምስኪኑ ልቤን ወስዳዋለች ይች ሰው

      ኦ…..ወስዳዋለች

      ወስዳዋለች

      Show more

      Playing Next