Playing Next....


      አያ ጎንደሬ | Aya Gondere ( Sami-Dan )



      ✔️ Click Here for More Musics

      አያ ጎንደሬ

      አያ ጎንደሬ አያ ጎንደሬ
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ

      ይህ ልቤ ከዛ ማዶ
      ቸገረው ሰው ወዶ
      እግሬን ይመራኛል
      ጎንደርን ይለኛል

      እንኳን የሰው ሊያምረው የሌላ መች ሊያይ
      ቢዚ ነው ጎንደሬ በራሱ ጉዳይ
      ስሟን እያነሳ ጠርቶ መች ጨረሰ
      ይዘምርላታል ባሩድ እያጨሰ

      ወተትሽን ጠጥቼ ማርሽን ብቀምሰው
      አንጀቴ ሳሳልሽ ፍቅር አይችልም ሰው
      በሚነዝረው ፍቅሩ እኔን ከተሜው
      አሳስሮ አስቀረኝ አይ የጎንደር ሰው

      ና ና
      ነይ ነይ

      እንዴት ነሽ (4x) እንደምነሽ እንዴት
      እንደምን ከርመሻል
      እንኳን ባይኔ አይቼሽ ባሳቤም ገስፈሻል
      የሳቅሽ ወገግታ የጨዋታሽ ቃና
      መልሶ መላልሶ ያመጣኛል ገና

      ኦኦ

      አያ ጎንደሬ አያ ጎንደሬ
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ

      ( አያ ጎንደሬ አያ ጎንደሬ
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ )

      አያ ያገር ልጅ አያ ያገር ልጅ
      ወገን እንደሌለው ቆሟል ከሰው ደጅ

      ( አያ ያገር ልጅ አያ ያገር ልጅ
      ወገን እንደሌለው ቆሟል ከሰው ደጅ )

      ለራሱ የማያንስ ለሰው የተረፈ
      ሲተክዝ አየሁት ችሎ እያለፈ
      ለሁሉም ምትበቃ አንድ ሀገር አስቦ
      አላስኬድህ አለው ሀገር ምድሩ ጠቦ

      ጎንደር ጎንደር ይላል ለካ ወዶ አይደለም
      ፍቅሯን የቀመሰ ከራሱም አይሆንም
      ስሟን እያነሳ ጠርቶ መች ጨረሰ
      ይዘምርላታል ባሩድ እያጨሰ


      አያ ጎንደሬ አያ ጎንደሬ
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ

      ( አያ ጎንደሬ አያ ጎንደሬ
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ )

      አያ ያገር ልጅ አያ ያገር ልጅ
      ወገን እንደሌለው ቆሟል ከሰው ደጅ

      ( አያ ያገር ልጅ አያ ያገር ልጅ
      ወገን እንደሌለው ቆሟል ከሰው ደጅ )

      አያ ጎንደሬ (2x)
      እያለ ይኖራል ኢትዮጵያ ሀገሬ



      Melody : - Sami-Dan x public
      ዜማ :- ሳሚ-ዳንና የህዝብ

      Lyric :- Sami-Dan
      ግጥም :- ሳሚ-ዳን

      Arrangement :- Sami-Dan
      ቅንብር :- ሳሚ-ዳን

      Tenor Sax :- Zerihun Belete
      ቴነር ሳክሲፎን: - ዘሪሁን በለጠ

      Bass Guitar :- Fassil Wehib
      ቤዝ ጊታር :- ፋሲል ውሂብ

      Lead Guitar :- Shilu ( Samuel Assefa )
      ሊድ ጊታር :- ሽሉ ( ሳሙኤል አሰፋ )

      Keyboard :- Tewnet
      ኪቦርድ :- ተውኔት

      Drum :- Addio (Addis Ras Band )
      ድራም :- አዲዮ ( አዲስ ራስ ባንድ )

      Masinko :- Degsew Abebe
      ማሲንቆ :- ደግሰው አበበ

      Mixing and Mastering :- Andy Bete Zema
      ሚክስንግና ማስተሪንግ :- ኤንዲ ቤተ ዜማ

      Background Vocal :- Esubalew Yitayew (Yeshi) | Henok Getachew | Kaleab Mulugeta | Tigabu Cherinet

      ተቀባይ ድምፅ :- እሱባለው ይታየው (የሺ) | ሔኖክ ጌታቸው | ቃለአብ ሙሉጌታ | ጥጋቡ ቸርነት

      Show more

      Playing Next