ሙና | Muna by Sami-Dan
✔️ Click Here for More
Musics
New Ethiopian Music 2018/2025
ሙና
ጊዜ ሁሉን ፈራጅ ጊዜ ትልቅ ዳኛ
ላይቆም ጥሎ ሄደ ሁሉን እያስተኛ
የትዝታን ገመድ ሚበጥሰው ጠፍቶ
አንጀቴን ፈተለው ባዝቶ ባዝቶ
ሰው መቼስ ደፋር ነው ካምላኩ ይጣላል
መፈጠር ነው እንጂ መፍጠር መች ይቀላል
ተመስገን ማለት ቀና ብሎ ላለው
ክፈሉኝ ለማይል ለምንተነፍሰው
አምናን ያሞግሳል ዘንድሮ ላይ ቆሞን
ሰው ሲበላ እያየ እሱ ቢያድር ፆሙን
ጥቂቱ እየበላ ሀገር ያድራል ፆሙን
ጠባሳዬን ሳየው ምስሉማ ባልከፋኝ
ጠባሳዬን ሳየው ምስሉማ መች ከፋኝ
የያዘውን ታሪክ መስማት ነው ሚጎዳኝ
ታሪኩን ነዉ እንጂ ማሰቡ ሚጎዳኝ
አንቺም ቀናተኛ እኔም ቀናተኛ
ብቻችንን ቀረን ጠፋና ቤተኛ
አንዲት ሰው ወደድኩኝ ከሁሉ አስበልጬ
እስከዘላለሜ ናትና አጣጬ
ሳናይ ያመነውን ሲሆልና ገነት
በምድር አመጣነው በውሸት በውነት
ሰላም መጣ ብዬ ቤቴን ስወለውል
ፍቅር ገባ ብዬ ደጃፌን ሳሳምር
ምነው ይሄ ልጅሽ ይወዳል ክርክር
ለዚህስ ከሆነ ባይወለድ ቢቀር
ጊዜ ያገነነው ለማቁሰል ቢችልም
ጡንቻ ያገነነው ለችጋር ቢጥልም
ሀገርን ፈፅሞ የገደለ የለም
ዘላለም ኗሪ ናት ባለም ሌላው የለም
እውነት ምንድነው ስትል ምላሴ
ተጨነቀች አንድ ነብሴ
ሞትስ ምንድነው ስትል ምላሴ
መልስ እያጣች አንድ ነብሴ
ባካል ከፊቱ ቆሞለት እንኳን አላየውም ያ ፒላጦስ
እውነት ምንድነው ብሎ ጠየቀው ተጋርዶበት ትልቁ መልስ
ሙና ሙና - ሙናዬ
በሰው ልጅ ሀሳብ ውስጥ በቃኝ ቢኖር ኖሮ
ማን ይናጥጥ ነበር ማንስ ተቸግሮ
ሀብታምና ደሀ አይ መጨረሻቸው
እንዳልተለካኩ አንድ ሆነ ሞታቸው
ሙና credit
Melody : - Sami-Dan
ዜማ :- ሳሚ-ዳን
Lyric :- Sami-Dan
ግጥም :- ሳሚ-ዳን
Arrangement :- Sami-Dan
ቅንብር :- ሳሚ-ዳን
Tenor Sax :- Ashenafi
ቴነር ሳክሲፎን: - አሸናፊ
Bass Guitar :- Jimmy ( Girma Moges )
ቤዝ ጊታር :- ጂሚ ( ግርማ ሞገስ )
Lead Guitar :- Shilu ( Samuel Assefa )
ሊድ ጊታር :- ሽሉ ( ሳሙኤል አሰፋ )
Keyboard :- Hybrid ( Habte )
ኪቦርድ :- ሀይብሪድ ( ሀብቴ )
Drum :- Addio (Addis Ras Band )
ድራም :- አዲዮ ( አዲስ ራስ ባንድ )
Mixing and Mastering :- Andy Bete Zema
ሚክስንግና ማስተሪንግ :- ኤንዲ ቤተ ዜማ
Background Vocal :- Esubalew Yitayew (Yeshi) , Henok Getachew , Kaleab Mulugeta, Tigabu Cherinet
ተቀባይ ድምፅ :- እሱባለው ይታየው (የሺ) , ሔኖክ ጌታቸው , ቃለአብ ሙሉጌታ ጥጋቡ ቸርነት
Show more
