Playing Next....


      "ምን ዋጋ አለው" ግርማ ተፈራ | "Min Waga Alew" Girma Tefera #visualizer #sewasewmultimed



      ✔️ Click Here for More Musics

      #girmatefera #minwagaalew #gin_yet_hager #visulaizer #sewasewmultimedia

      -----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

      ምን ዋጋ አለው

      ወደ ኋላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
      የትላንቱ ትውልድ የ ዛሬን ቢወቅሰው
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
      ወደ ኋላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
      የትላንቱ ትውልድ የ ዛሬን ቢወቅሰው
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
      ////
      ለመራራም ይሁን ለጣፋጩ ፈሬ
      የ ትላንቱ ችግር ምክንያት ነው ለ ዛሬ
      ቅብብል ነዉና የ ትውልድ ጉዞ
      የዛሬዉም ነገር ይወልዳል አርግዞ
      /////
      ምርቃቱን ያሰማን አይጠቅምም እርግማን
      ማምስገን ማድነቅን ዛሬ እስካላወቅን
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አልው
      ////
      ዘመን ሲነሳ ሁሌ ወቀሳ
      ያደፈርሳል ንጹህ ፍቅር
      ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር
      ////
      የፊተኛው አልፎ የ ኋላው ሲተካ
      ሁሉም በ አንድ ሚዛን አይችልም ሊለካ
      ተግባሩ ሲመዘን ቢለይም መጠኑ
      የራሱ ልክ አለው ሁሉም በ ዘመኑ
      ያኛው መሰረት ጥሎ ይሄኛው አስቀጥሎ
      መጪው እንዲጨርሰው ፍቅሩን ካላወረሰው
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አልው

      ወደ ኋላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
      የትላንቱ ትውልድ የ ዛሬን ቢወቅሰው
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
      /////
      ሰጪም ተቀባይም በየበኩላቸው
      በ ቅደም ተከተል ድርሻ ድርሻ አላቸው
      ሰጪም በ ሰጠው ልክ ከተመዘነበት
      ያጎደለው ካለ እሱም እዳ አለበት
      ሁሉም እራሱን መርምሮ ከ ስህተቱ ተምሮ
      ዛሬን እየቀየረው ነገን ካላሳመረው
      ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው
      /////
      ታሪክ ሲወሳ ትውልድ ወቀሳ
      ያቀዘቅዛል የሞቀን ፍቅር
      ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር
      ////
      ዘመን ሲነሳ ሁሌ ወቀሳ
      ያደፈርሳል ንጹህ ፍቅር
      ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር
      ////
      ያደፍረሳል ቀጣዩን ፍቅር
      ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር


      -----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
      ምንም አይነት ቪዲዮ እንዳያመልጥዎ ሰብስክራይብ ያድርጉ እና ማሳወቂያዎችን ያብሩ 🔔
      Subscribe and turn on notifications 🔔 so you don't miss any videosadmin

      ይህን ሊንክ በመጠቀም ሰዋሰው መተግበሪያን ያገኙታል 📱
      Use this link to get Sewasew Multimedia 📱
      https://onelink.to/mubp9y


      ከእኛ ጋር ጊዜዎን ይቆዩ | Stay Connected with us
      Facebook : https://www.facebook.com/sewasewmultimedia
      Instagram : https://www.instagram.com/sewasewmultimedia
      Linkedin : https://www.linkedin.com/compa....ny/sewasew-multimedi
      Twitter : https://twitter.com/sewasewMmedia
      Tiktok : https://www.tiktok.com/@sewasewmultimediaet
      YouTube : https://www.youtube.com/@sewasewmultimedia
      Telegram : https://t.me/sewasewmultimedia

      #sewasew #sewasewmultimedia #creativity #ignitingcreativity #creativeeconomy


      Unauthorized use, distribution, and re-upload of this content is strictly prohibited
      Copyright 2023, ©Sewasew Multimedia. All rights reserved.

      Show more

      Playing Next