Playing Next....


      Jonny Ragga - Yiresashal Woy (Esat ) | ጆኒ ራጋ - ይረሳሻል ወይ (እሳት) - Track 2 - New Ethiopian Music 2025



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga - Yiresashal Woy (Esat)
      ጆኒ ራጋ - ይረሳሻል ወይ (እሳት)

      Track 2 of 7 from the Album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Esat

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Tandra (@mixedbylytes) Jhagrooatat at Mixing Lab (JAMAICA)
      Mastering: Ben Dubstation (FRANCE)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _______________________________________

      የትዝታ ባቡር በትውስታ ፉርጎ
      ሊወስደኝ ከቦታው በጊዜ ሃዲድ ላይ ተመልሶ ሄዶ

      በሃሳብ ተጉዞ ያሳለፍነው ዘመን ላይ ማረፊያውን አርጎ

      አንዳንዴ ይሰለቻል አሁን እና እዚህ
      ካልጎበኘን ሄደን ያን የፍቅር ጊዜ

      ይረሳሻል ወይ ያኔ ሆነን አፍላ
      የምንውልባቸው ድብቅ ስፍራ

      ተሞልተን በሃሴት፣
      ስናሳልፍ ደስ የሚል ጊዜ

      መሆናችን ባዶ ኪስ ሳያግደን
      በንፁህ ልቦና ብቻ ተዋደን

      ሆነሽ የአፍላ ፍቅሬ፣
      'ማይረሳ ስሜት ነው እስከዛሬ

      በዘመኑ ፋሽን ሆነን ዘንጠን
      ጭፈራ ቤት ገብተን ደስታውን መርጠን

      እረስተነው ዘና፣
      ሚጠብቀንን ቁጣ እና ዱላ

      እንጫወት እስኪ እያልን ሻይ ቡና
      ተጉዘን በትዝታ ወደ ኋላ

      ጊዜውን መልሰን፣
      የወጣትነት ዘመንን አስታውሰን

      ቀሪ እጣፋንታውን መወሰን በእጁ ቢሆንም ለሰው
      ያለፈው ግን ታሪክ ሆኗል በፍፁም የማይመልሰው

      ያሳለፍነው ዘመን ቢሆንም መልካም ሆነ መናኛ
      ወይ 'ሚሆነው ነው መማሪያ ወይ ለህይወቱ መፅናኛ

      ላስበው ላንዳፍታ፣
      ሄጄ በትውስታ

      ወረትን ጊዜ እያበጠረ፣
      ይቀራል ወዳጅ የጠጠረ

      ልቃኘው ወይ ላፍታ፣
      ተመልሼ ቦታው

      ጊዜው ቢርቅ ቢገፋም፣
      ትዝታ እንደሰው ጥሎ አይጠፋም

      ይረሳሻል ወይ ያኔ ሆነን አፍላ
      የምንውልባቸው ድብቅ ስፍራ

      ተሞልተን በሃሴት፣
      ስናሳልፍ ደስ የሚል ጊዜ

      መሆናችን ባዶ ኪስ ሳያግደን
      በንፁህ ልቦና ብቻ ተዋደን

      ሆነሽ የአፍላ ፍቅሬ፣
      'ማይረሳ ስሜት ነው እስከዛሬ

      በዘመኑ ፋሽን ሆነን ዘንጠን
      ጭፈራ ቤት ገብተን ደስታውን መርጠን

      እረስተነው ዘና፣
      ሚጠብቀንን ቁጣ እና ዱላ

      እንጫወት እስኪ እያልን ሻይ ቡና
      ተጉዘን በትዝታ ወደ ኋላ

      ጊዜውን መልሰን፣
      የወጣትነት ዘመንን አስታውሰን

      ጀማው ሁሌም ስሜቱ ሬጌ
      ጀማው ከዱሮም ሙዱ ራጋ

      በልጅነት ተከትቦ ራጋ ማፊን በደሙ
      አንበሳ አርማው፣ አረንጓዴ ነው ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ

      ለጀማው ይድረስ ምስጋና የሰጠው ድጋፍ ለህልሙ
      አይኖርም ነበር ዛሬ ጃኒ ራጋ ስሙ

      በኩዊንስ እና ታናል አርገን ኢግዚቢሽን ማዕከል
      ራምጃም እና ኮፊ ሃውስ የጨበጥኩበት ማይኩን

      ፒኮክ ቀበርቾ አምሽቶ ወደቡፌ ደ ላጋር
      ሸበላ ቆነጃጅቱ፣ ሊዝናኑ ከኛ ጋር

      የዛን አፍላ ህልም ይዘነው ለህይወት ጉዞ ወተናል
      መከራ የሞላው ነው መንገዱ ብዙ ወዳጆች አተናል

      ጥሩ ጊዜ ትውስታን ትቶ መጥፎው ያልፋል ጠባሳ
      ዛሬ አብረን የዘለቅነው ብርጭቆአችንን እናንሳ

      ጀማው ሁሌም ስሜቱ ሬጌ
      ጀማው ከዱሮም ሙዱ ራጋ

      ላስበው ላንዳፍታ፣
      ሄጄ በትውስታ

      ወረትን ጊዜ እያበጠረ
      ይቀራል ወዳጅ የጠጠረ

      ልቃኘው ወይ ላፍታ
      ተመልሼ ቦታው

      ጊዜው ቢርቅ ቢገፋም
      ትዝታ እንደሰው ጥሎ አይጠፋም

      ላስበው ላንዳፍታ፣
      ሄጄ በትውስታ

      ወረትን ጊዜ እያበጠረ
      ይቀራል ወዳጅ የጠጠረ

      ልቃኘው ወይ ላፍታ
      ተመልሼ ቦታው

      ጊዜው ቢርቅ ቢገፋም
      ትዝታ እንደሰው ጥሎ አይጠፋም

      Show more

      Playing Next