Jonny Ragga - Yemanat Konjo (Wiha) | ጆኒ ራጋ - የማናት ቆንጆ (ውሃ) - New Ethiopian Music 2025
✔️ Click Here for More
Musics
Jonny Ragga - Yemanat Konjo (Wiha)
ጆኒ ራጋ - የማናት ቆንጆ (ውሃ)
Track 7 of 8 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha
Lyrics: Jonny Ragga
Melody: Jonny Ragga
Arrangement: Jonny Ragga
Producer: Jonny Ragga
Mixing: Nicolas SÉLAMBIN at 129H STUDIO (FRANCE)
Mastering: Sébastien «Mellow Mood » Houot at Wise Studio (FRANCE)
© 2025 All Rights Reserved
Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.
_________________________________________
የመጀመሪያ ቀነ ያኔ ገና ሳያት
ፈገግታዋ ቸር ሆኖ አይኗንም ከዓይኔ ያዝኩት
ምናልባት እሷም በድብቅ
ትወደኝ ይሆን እንዴ
ጥላቻ ለኔ የላትም፣
ባይሆን ግን ደስ ብላት ነው አልኩኝ
ይሄ ድሬድ ላክስ
ድሬድ ላክስ ድሬድ ላክስ ራስታ
በጣም ወዶሻል
ለአንድ ቀን አዳር
ለአንድ ቀን ብቻ ውሎ
እንዴት ይመስልሻል
እስትንፋሴ ከስጋዬ ሲለያዩ እኔም ያኔ ነው አንቺን የምለየው
እናም አንቺ ካለሽ ለኔ የፍቅር ስሜት ይውጣ ይታይ አትሸሽጊው
ከወደድሺኝ ከወደድሺኝ ልቤን እንኪ እንቺ ያንቺው ነው
ከፈለግሺኝ ካፈቀርሺኝ እንሆ ደጅሽ ቆሚያለሁ
የማናት ቆንጆ፣ ቆንጆ
እናቷ ናቸው ኩሩ ፈጣሪን የሚፈሩ
የጎረቤት ወጣት የሚገሩ
የማናት ሸጋ፣ ሸጋ
አባቷ የተማሩ ተግባቢ ናቸው
ጥሩ የሚወደዱ በሰፈሩ
የማናት ቆንጆ፣ ቆንጆ
ወንድም እና እህቶቿ ፊደል የቆጠሩ
ጨዋ ቤተሰብን ያሰከበሩ
የማናት ሸጋ፣ ሸጋ
አስተዳደጓን አይቶ መገመት ይቻላል
ወላጆቿ ንግስት ያፈሩ
ቃልኪዳን ልግባልሽ ያዢ ማስታወሻ
ስሚ ስሚ ስሚ ስሚ
Jonny Ragga
Tell dem tell dem
እንደ እናትሽም ባላኖርሽ እምላለሁ እንደ-ማልተኛ
እስክንገነባው የኑሮን ማማ ባንቺ ምቾት ከፍታ
ቃል እገባለሁ ልጠብቅሽ ሆኜ ባባትሽ ቦታ
እንደ ጥይት መከላከያ ጃኬት ሆኜልሽ መከታ
እንደ አንድ ሆኖ ምሎ ልባችን ተስማምቶ ችሎ እስኪመታ
ተዋህደን በሙሉ ስሜት በከንቱ ወሬ ላንፈታ
እንደ ፈቃድሽም ልኖር ፍፁም ከቃልሽ ላልወጣ
ቃሌን በተግባር ላሳይሽ ልቤ እንደሚወድሽ በጣም
አለብኝ አደራ ሆድሽ እንዳይብሰው
ሲበረታ ሀዘንሽ እንባሽን ላብሰው
በፍፁም አልሻም መቼም ከፍቶሽ እንዳይ
No woman no cry
ከዛ ሁሉ በፊት ግን ከዛ ሁሉ በፊት
መመዘኔ አይቀርም ቀርቤ ወላጆችሽ ፊት
ባገኝ የነሱን ፍቃድ እሻለው በግሌ
በቃልኪዳን እንጣመር ልላክ ሽማግሌ
የባህሉን አርገን ሳናጎል ወግ ልምዱን
ንገሺ በልቤ ላይ ልድፋልሽ ዘውዱን
ንጉሥሽ አርጊኝ ሁኚልኝ ንግሥቴ
እኔም ልሁን ራስ ልብ ሁኚ ለቤቴ
ንጉሥሽ አርጊኝ ሁኚልኝ ንግሥቴ
እኔም ልሁን ራስ ልብ ሁኚ ለቤቴ
የማናት ቆንጆ፣ ቆንጆ
እናቷ ናቸው ኩሩ ፈጣሪን የሚፈሩ
የጎረቤት ወጣት የሚገሩ
የማናት ሸጋ፣ ሸጋ
አባቷ የተማሩ ተግባቢ ናቸው ጥሩ
የሚወደዱ በሰፈሩ
የማናት ቆንጆ፣ ቆንጆ
ወንድም እና እህቶቿ ፊደል የቆጠሩ
ጨዋ ቤተሰብን ያሰከበሩ
የማናት ሸጋ፣ ሸጋ
አስተዳደጓን አይቶ መገመት ይቻላል
ወላጆቿ ንግስት ያፈሩ
Show more
