Playing Next....


      Jonny Ragga - Wiha Ena Esat (Esat) | ጆኒ ራጋ - ውሃ እና እሳት (እሳት) - New Ethiopian Music 2025



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga - Wiha Ena Esat (Esat )
      ጆኒ ራጋ - ውሃ እና እሳት (እሳት)

      Track 4 of 7 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga & Dawit Nigusse
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Kirubel Tesfaye at Tora Studio (ETHIOPIA)
      Mastering: Kirubel Tesfaye at Tora Studio (ETHIOPIA)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _________________________________

      ከፍጥረቱ ጀምሮ ለሰው ልጅ
      ለኑሮው አስፈላጊ ሃይል ናቸው

      አመጣጥኖ ይጠቀምባቸው ዘንድ
      ጥበብም በእጁ ናት

      አማካዩን ሲሻ ለኑሮው ዋስትና፣
      የዘነጋም ጊዜ መጥፊያው የሚሆኑ

      ውሃ እና እሳት

      ቤታችን ሰላም ከሆነ ከመነሻው 
      መከራም በዝቶ ቢከፋም እንዳሻው

      በአንድ ላይ መቆማችን ሲያበረታን
      ፈተናው ከጋራ ጉዞ አይገታን
       
      ኦሆሆሆኦሆ 
      የተናቀ ክብር

      ኦሆሆሆኦሆ 
      የግብዝ ክምር

      እንዴት ነው ይሄን ሁሉ ታሪክ የሰራነው
      ማነው ወደዚህ ህሊና ማጥ የመራን

      እንዴት እንጓዝ ወደ ፊትስ አብረን
      ካልቆምን ዛሬ ልዩነቱን ሰብረን

      ኦሆሆሆኦሆ - የተቀጣ ሹመት
      ኦሆሆሆኦሆ - የወረደ ልቀት

      ኦሆሆሆኦሆ - የስቃይ ምቾት
      ኦሆሆሆኦሆ - ማይሰማ ጸሎት

      መቻቻል እያለ ታዲያ የምን መፈታተን
      ተከባብሮ የመኖር ፀጋን ወደ ጎን ትተን
      ከቶ ለምን ስቃዬን ትወዳለህ
      እንጨቱንስ በቁስሌ ትሰዳለህ

      ደርሶ የአዋቂነት ካባ ግብዝ ሲላበስ
      የዕውነት መለኪያው ሊዛባ ዕውቀት ሊወቀስ

      ፍቅር አቅሉን ሲስት ክብር ሊራከስ
      ማቀፍ ይሆናል ማነቅ መሳምም መንከስ

      ጥላቻ ፍቅር ለይቶ መልኩን 
      ተረስቶ ጥበብ የሰው ልኩ

      ከሌለ አማካኝ ሀሳብ ለመስማማት
      ፅንፍ ሆኖ ይቆማል ዘብ ለክፋት

      እንደ ውሃ እና እሳት
      እንደ ውሃ እና እሳት

      እየኖሩ አብረው በአንድ ጣራ
      ፈጥረው ልዩነት ገደቡ ያልጠራ

      እየተገፋፉ አቋም መሳት 
      ራስን ለማዳን አብሮ መጥፋት

      እንደ ውሃ እና እሳት
      እንደ ውሃ እና እሳት

      እንደ ውሃ እና እሳት
      እንደ ውሃ እና እሳት

      የተኛው ውቂያኖስ ነውጡን ተሸክሞ 
      በውስጡ ያሉትን ንፍሳት ጩኸት አፍኖ

      በላዩ ሰላም አስፍኖ እያዳፈነ ማዕበል
      ያሰቀጥላል ህይወት ንፋሱን በማባበል

      ባህሪው አንድ ነው አመድ ካዳፈነው እሳት
      የከሰመ እስኪመስል አይንን በማሳሳት 

      ከተነሱ ሁለቱም ሰው አይተርፍም ከጥፋት
      ሲመጠን ሀይላቸው ግን ናቸው የሰው ትሩፋት

      ሆዱን ሞልቶ ህሊናው የተራበ
      ኦሆ ዘንጦ ልቦናው የታወረ

      ባህል ታሪክ ወግና ስርአት ዕምነቱ
      የማንነቱ ውል የአንድ ህዝብ ዕውነቱ

      ጠርዝ ረገጡ ጥራዝ ነጠቅነትን ሲላበስ 
      አዋቂ ነኝ ባዩ እንደ አሸን ሞልቶ ሲታፈስ


      ህሊና ነቅቶ ከሌላ ተወቃሽ
      አውራው አንቀላፍቶ ጫጩቱ ቀስቃሽ

      ጥላቻ ፍቅር ለይቶ መልኩን 
      ተረስቶ ጥበብ የሰው ልኩ

      ከሌለ አማካኝ ሀሳብ ለመስማማት
      ፅንፍ ሆኖ ይቆማል ዘብ ለክፋት
                       
      እንደ ውሃ እና እሳት
      እንደ ውሃ እና እሳት

      እየኖሩ አብረው በአንድ ጣራ
      ፈጥረው ልዩነት ገደቡ ያልጠራ

      እየተገፋፉ አቋም መሳት 
      ራስን ለማዳን አብሮ መጥፋት

      እንደ ውሃ እና እሳት
      እንደ ውሃ እና እሳት

      Show more

      Playing Next