Playing Next....


      Jonny Ragga - Tewedaj (Wiha) | ጆኒ ራጋ - ተወዳጅ (ውሃ) - New Ethiopian Music 2025



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga - Tewedaj (Wiha)
      ጆኒ ራጋ - ተወዳጅ (ውሃ)

      Track 3 of 8 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Nicolas SÉLAMBIN at 129H STUDIO (FRANCE)
      Mastering: Sébastien «Mellow Mood » Houot at Wise Studio (FRANCE)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _________________________________________

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ፣ ውበቷ ከሩቅ ጠሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ከመቼው ልቤን ረታ

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ ናፍቆቷ ከልብ ቀሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ፍቅሯ አይሰጥም ፋታ

      እንደ አልማዝ ናት እንደ እንቁ
      የትሰርቅ ሃሳብ ገና ከሩቁ

      እኔ አልቻልኩም ዓይኔን ለመንቀል
      እሷ ሀይል አላት ስቦ የሚያስቀር

      ብቅ ስትል ገና ከአደባባይ
      የሁሉም ቀልብ ያርፋል እሷ ላይ

      ዓይኗም ተኮሳትሮም ናት አባባይ
      በእርግጥ ፍፁም አማላይ

      ፀጉሯን ሳየው በአየር ላይ ተገልቦ
      እየዋኘ በንፋስ ታጅቦ

      ከትከሻዋ አርፎ ደሞ ሲበተን
      ደርሶ ልቤ ሊፈተን

      ግብግብ ይዤ ልደብቅ ስሜቴን
      የግድ ሆኖበት ቢያሳብቅም ፊቴ

      ሳልነግራት ኋላ ከንቱ ነው ልፋቴ

      ላውራት በልኳ በጨዋነት መልኳ
      ስርዓት ትሻለች አታውቅም ፌዝ እንኳን

      አታስነካም ልኳን

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ፣ ውበቷ ከሩቅ ጠሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ከመቼው ልቤን ረታ

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ ናፍቆቷ ከልብ ቀሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ፍቅሯ አይሰጥም ፋታ

      ዬዬዬ ወቸው ጉድ...

      መልኳ ብቻ አይደለም ሰጥቷታል ፀባይ
      አቋሟን ያየ ይፈዛል ኑሮዋ የዘበናይ

      ያሳደጋት ጨዋ ከባለጌው ማትታይ
      ከዚህ አለም አይደለች የተባረከች ከላይ

      ያዝኳት አይኗን ከዓይኔ ላይ
      ምናለ የልቤን ባልኳት፣ የመውደዴን ጉዳይ

      ቢሆን ነው ልቤ ቢያምናት አትመስልም በዳይ
      የሷም ልብ የፈቀደ ይመስላል ምላሿን እንዳይ

      ቢሆንም ለአንድ አፍታ አይቼ አንዴ ባወራት
      ብጋብዛት ምሳ ይመሽ ይሆናል ለእራት

      እሷም ጠልቃ ብታይ ስለእኔ ፍንጭ ቢኖራት
      ውስጤንም እንድታውቅ ስሜቴም እንዲነግራት

      የዋዛ አይደለም እስክስታና ዳንሷ
      ሰውነቷ ታዛዥ ለሬጌና ዳንስሆል

      በሁሉም ሙያ አታውቅም ከሌላ አንሳ
      ባላንጣዎቿን ሁሌ አሳፍራ መልሳ

      አርቴፍሻል ውበት የላት አታጌጥም ተውሳ
      ባያት ሰው ተወዳጅ የሆነች ወላንሳ
      እስኪ አሁን ንገረኝ ማን ነው የማይወዳት

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ፣ ውበቷ ከሩቅ ጠሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ከመቼው ልቤን ረታ

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ ናፍቆቷ ከልብ ቀሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ፍቅሯ አይሰጥም ፋታ

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ፣ ውበቷ ከሩቅ ጠሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ከመቼው ልቤን ረታ

      ተወዳጅ ናት ተፈቃሪ ናፍቆቷ ከልብ ቀሪ
      ገና ባያት ለአንድ አፍታ ፍቅሯ አይሰጥም ፋታ

      Show more

      Playing Next