Playing Next....


      Jonny Ragga feat Yohana - Bithejim (Wiha) | ጆኒ ራጋ ከዮሐና ጋር - ብትሄጂም (ውሃ) - New Ethiopian Music 2025



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga feat Yohana - Bithejim (Wiha)
      ጆኒ ራጋ ከዮሐና ጋር - ብትሄጂም (ውሃ)

      Track 2 of 8 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Nicolas SÉLAMBIN at 129H STUDIO (FRANCE)
      Mastering: Sébastien «Mellow Mood » Houot at Wise Studio (FRANCE)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.
      _________________________________

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      መች ሆነ ሰው እንዳወራው
      አልደረሰም ልቤ የፈራው - ኑሮ

      ቀኑ አሁንም ይነጋል ይመሻል
      (የማናት ተዋናይ)
      መች እንዳንቺ ጥሎ ይሸሻል
      (ተለዋዋጭ ስብዕና እንደ አየሩ ፀባይ)
      ዞሮ ዞሮ ለኔም ይዟል መካሻ
      (እኔስ ለሷ ነበርኩ ሆደ ሰፊው ሰማይ)

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      መች ሆነ ሰው እንዳወራው
      አልደረሰም ልቤ የፈራው - ኑሮ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      አልሳተም ህይወት ሚዛኑን
      አልፎታል ልቤም ሃዘኑን - ዱሮ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      መች ሆነ ሰው እንዳወራው
      አልደረሰም ልቤ የፈራው - ኑሮ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      አልሳተም ህይወት ሚዛኑን
      አልፎታል ልቤም ሃዘኑን - ዱሮ

      ልቤ ላንቺ ራሱን ሲሰጥ በፍፁም ከስስት ርቆ
      ታዘብኩት ታዘብኩት ልብሽን ሲሳብ በዕንቁ
      የጠየቅሺኝን ሁሉ ባረኩ ለፍቅርሽ ቀልጬ እንደጧፍ
      መንታ ልብሽ ልብሽ ሆኖ በቋፍ

      አምናለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      አልክድም ሃዘን ጭንቀት ናፍቆቴን
      ይኸው ጊዜም ዛሬ ሽሮት
      ማን ሊያምነው

      አውቃለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      ገሃድ ነው በፍቅርሽ መጎዳቴ
      ዛሬን ሊያልፈው ልቤ ችሎት
      እላለሁ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      መች ሆነ ሰው እንዳወራው
      አልደረሰም ልቤ የፈራው - ኑሮ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      አልሳተም ህይወት ሚዛኑን (Ragga Jonny)

      አልፎታል ልቤም ሃዘኑን - ዱሮ

      Well well, እኔስ ምን ልበል
      ሃሳቤ ሩቅ ነበር፣ አልጠበኩም እንዲህ በአጭር ሊቀር
      ህልሜ ሊሰበር፣ ትልሜ ሊቀበር
      አስቤአት ነበር ለብዙ - ለብዙ ቁምነገር

      መች መስሎኝ በሌላ መውደዴ ይተካል
      አስቤ እንድንሆን አንድ አምሳል አንድ አካል
      ብዬ ሁሉም ደህና ከእሷ ጋር ይሳካል
      ጥላኝ ልትሄድ አጥፋ የራሷን ቃል

      አዝናለሁ ሳረዳሽ፣ ሆነሽ ኬረዳሽ፣
      ብትሄጂም እንደተጎዳሽ
      ልቤ አግኝቷል ምላሽ፣ አንቺን የምትተካሽ፣
      ምትሆነኝ የልብ አዳሽ

      ሞኝ ናት ተላላ፣ ፍቅሩን የሰጣት ልቡን ብላ ችላ
      እንደጋሻ ጃግሬ ልሁናት ከለላ
      ያላትን አፍቃሪ ሞልታ ሽንገላ፣
      ስቃ በይስሙላ፣ በውሸት መሃላ ብትሄድም ጥላ
      ነን ጆኒ ራጋና ዮ-ዮሐና፣ ባለችበት እሷም ትሁን ደህና

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      መች ሆነ ሰው እንዳወራው
      አልደረሰም ልቤ የፈራው - ኑሮ
      ድሮም ግልፅ ነበር ልብሽ እንዳልረካ

      ብትሄጂም ትተሺኝ
      አልሳተም ህይወት ሚዛኑን
      አልፎታል ልቤም ሃዘኑን - ዱሮ
      በእቅፌ ሆነሽ እንኳን ሃሳብሽ ሌላው ጋ

      ቀኑ አሁንም ይነጋል ይመሻል
      መች እንዳንቺ ጥሎ ይሸሻል

      አምናለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      አልክድም ሃዘን ጭንቀት ናፍቆቴን
      እኔ አላነሳም ስምሽን በሐሜት
      ቂም የለኝም ወይ የበቀል ስሜት

      አውቃለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      ገሃድ ነው በፍቅርሽ መጎዳቴ
      አንዱ በው ሲዘጋ ሌላ ይከፈታል
      ልቤም ምላሹን አግኝቷል

      አምናለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      አልክድም ሃዘን ጭንቀት ናፍቆቴን
      እኔ አላነሳም ስምሽን በሐሜት
      ቂም የለኝም ወይ የበቀል ስሜት

      አውቃለሁ ስትሄጂ መጎዳቴን
      ገሃድ ነው በፍቅርሽ መጎዳቴ
      አንዱ በው ሲዘጋ ሌላ ይከፈታል
      ልቤም ምላሹን አግኝቷል

      Show more

      Playing Next