Playing Next....


      Jonny Ragga feat Nhatty Man - Alat Liyu Gudai (Esat) | ጆኒ ራጋ ከናቲ ማን ጋር - አላት ልዩ ጉዳይ (እሳት)



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga feat Nhatty Man - Alat Liyu Gudai (Esat)
      ጆኒ ራጋ ከናቲ ማን ጋር - አላት ልዩ ጉዳይ (እሳት)

      Track 3 of 7 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Esat

      Lyrics: Jonny Ragga and Nhatty Man
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Ben Dubstation (FRANCE)
      Mastering: Ben Dubstation (FRANCE)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _______________________________________

      This is a special collab you know
      Legendary Jonny Ragga alongside Nhatty Man

      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል
      ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን

      ከመድረሷ ገና ቦታው ድባቡ ይለወጣል
      ሁለመናዋ ውበት ታጥቆ ወጥታለች ምርኮ ለመጣል
      ከፀጉር እስከ ጥፍሯ ድረስ ቁንጅናዋ ፍጹም አይጣል
      ያያትም ላፍታ ወዶም ግኔታው ወዲያው እጅ ይሰጣል

      አሎሎ ዓይኗ ሲንከባለል
      ተከትሎ የኔም ሊዋልል
      ችቦ ወገቧ እንደ እርጎ ይናጣል
      አካባቢውም አብሮ ይናወጣል

      ጥርሷ በረዶ ነው ቤት ያደምቃል
      ፈገግታዋ ደምቆ ልብ ይሰርቃል
      ገና ሳያት ውበቷ አብሮ
      ሊመታ ልቤ እንደ ከበሮ

      እሷ አላላላላላት እሷ አላት ልዩ ተልዕኮ
      ያደፈጠ ውበቷን ታኮ
      አፍዞ ለመጣል ምርኮ
      እሷ አላላላላላት ልጅቷ አላት ስውር ጉዳይ
      ዕምባው ነው ግብሩ የተበዳይ
      ልቡን ሰብራ የምትጥል ግዳይ

      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል
      ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን

      ለዛ ያለው ሲስቅ ሲጫወት 
      ከብዙ አንድ ነው እንዲህ ያለ ውበት
      በመልኳ ወጥመድ ሁሉን አስጋሪ
      የወደዳትን እንባ አስገባሪ 

      ልጅቷ አመሏ ልዩ ነው
      ፀባይዋ ውበቷ ገዳይ ነው
      ገላዋ መለኛም ዘዴኛም ነች
      ጉብሏ የማትጠላ

      ቀርቦም አይቶ አውግቷት አብሮ ውሎ
      ወላፈኗ ያልነካው ቢመስልም ችሎ 
      ያልተረታ ማን አለ በሷ መውደድ
      በየተራ ተራ አንድ በአንድ

      ፓ - ፓ - ታ- ታ
      ምላጭ ስባ ቃታ 
      ገዳይ ነች ቀን ማታ
      አትሰጥም ፋታ 
      ስንቱን ጣለችው ከእግሯ ስር
      የዋዛ አይደለም የሷስ ፍቅር ’

      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አይችሏትም በስታይል አይችሏትም በፋሽን
      አላየሁ ሌላ ሴት ከሷ የምትሻል
      ሸልሟት ለድሏ የማራኪ ኒሻን
       
      ሞሳድ ነች CIA ወይ ደሞ ኬጂቢ
      ስልጣኑን የሰጣት ይዛለች አጃቢ
      ጆኒ ራጋ ናቲ ማን ሚስጥሯን ዘጋቢ
      ብዙ ነው ታሪኳ ፋይሏ መቶ ጂቢ

      አሎሎ ዓይኗ ሲንከባለል
      ተከትሎ የኔም ሊዋልል
      ችቦ ወገቧ እንደ እርጎ ይናጣል
      አካባቢውም አብሮ ይናወጣል

      ጥርሷ በረዶ ነው ቤት ያደምቃል
      ፈገግታዋ ደምቆ ልብ ይሰርቃል
      ገና ሳያት ውበቷ አብሮ
      ሊመታ ልቤ እንደ ከበሮ

      እሷ አላላላላላት እሷ አላት ልዩ ተልዕኮ
      ያደፈጠ ውበቷን ታኮ
      አፍዞ ለመጣል ምርኮ
      እሷ አላላላላላት ልጅቷ አላት ስውር ጉዳይ
      ዕምባው ነው ግብሩ የተበዳይ
      ልቡን ሰብራ የምትጥል ግዳይ

      እሷ አላላላላላት እሷ አላት ልዩ ተልዕኮ
      ያደፈጠ ውበቷን ታኮ
      አፍዞ ለመጣል ምርኮ
      እሷ አላላላላላት ልጅቷ አላት ስውር ጉዳይ
      ዕምባው ነው ግብሩ የተበዳይ
      ልቡን ሰብራ የምትጥል ግዳይ

      Show more

      Playing Next