Playing Next....


      Jonny Ragga feat. Eden Ayseshim - Ticheh Endalhed (Wiha) | ጆኒ ራጋ ከኤደን አይሸሽም ጋር - ትቼህ እንዳልሄድ (ውሃ)



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga feat Eden Ayseshim - Ticheh Endalhed(Wiha)
      ጆኒ ራጋ ከኤደን አይሸሽም ጋር - ትቼህ እንዳልሄድ(ውሃ)

      Track 6 of 8 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Wiha

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: Nicolas SÉLAMBIN at 129H STUDIO (FRANCE)
      Mastering: Sébastien «Mellow Mood » Houot at Wise Studio (FRANCE)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _________________________________________

      ለሰማው ሰው አፈታሪክ ቢመስልም
      ከልብ የኖረ ፍቅር አይከስምም

      በዓይን የገባው አለው ቦታ
      የመጀመሪያዋ ዕይታ

      ራጋ ማፊን ጃኒ ራጋ
      ኤዲን ይዟት የማይኩ አጋር - እኮ በይ

      ዝምተኛ መሆኑ ከዱሮ ሁሉም የሚያውቀው (ዕውነት ነው)
      መች ሆነና ሌላ ልቤን ስንት የሰረቀው

      ሲታገል እያየሁት ስሜቱን ከኔ ሊደብቅ
      አላስችል ብሎት መዋሸት ዓይኑ ፍቅሩን ሲያሳብቅ

      ብዙም ቃላት ባይወጣው ካፉ ፍቅሩ በድርጊቱ ይገለፃል
      ልቤም ጥርጣሬውን ትቶ መልሶ እምነቱን ያንፃል

      ችሎም ባይናገረው ቃሉን ትኩስ ነው ስሜቱ ይፋጃል
      ዓይኑ ሚስጥር አያውቅ ፍቅሩን ገሃድ ያውጃል

      ልሄድ ፈልጌ ሳመነታ ደሞም ያባብለኛል ዓይኑ
      ፍፁም እንድለየው አይሻም ላፍታ እንድ ርቀው ከጎኑ

      ለኔ ያለው ስሜቱን ማወቁ ሰጥቶት ለልቤ ትልቅ ተስፋ
      ቢያገኘው ፍቅሩን ሆኖ ሚዛን የሚደፋ

      ትቼህ እንዳልሄድ ሆኖ ስሜቴን መካድ
      እንዳልቆይ አብሬህ አጣሁት ያንተን ፈቃድ

      ስሜትህን ለመግለፅ ፍርሃትህ ካገደህ
      ካሳየኸኝ ፍቅር ድፍረትህ እየካደህ

      ልለይህ አልሻም ልቤ እየወደደህ (አምናለሁ)
      እየወደደህ

      እኔ ልናገር
      ስሚኝ...

      እንደመብረቅ ብልጭታ ነው ዓይንሽ ካይኔ የገባው
      እንደነጎድጓዱ ፍንዳታ ስሜቴ ያስተጋባው

      ጊዜ አላጠፋም ልቤ ፍቅርሽን ሊግባባው
      ሊነጠፍ እንደቄጠማ ከልብሽ ያደባው

      ለኔ ቢልሽ ነው፣ ልቤ የግልሽ ነው፣
      ከእጄ ቢጥልሽ ነው የፍቅር አምላክ

      ብሎ እጣፋንታሽ ነው፣ እኔ እንዳላጣሽ ነው፣
      ልሆን መከታሽ ልብሽ ወደእኔ ሲላክ

      አተኩሬ ዓይንሽን ሳይ ፈልጎ መሸሻ
      ይዞኝ ገባ ዞሮ ከሚያርፍበት የፍቅር ዋሻ

      ዓይናችን ተመሳጥረው በፍቅር ሆነው አቻ
      ሳናቀው እኛ ፈፅመው በስሜት ጋብቻ

      ተግባር ይናገራል ከሺ ቃላት በላይ
      ጥልቅ ነው መልዕክቱ ከሚሰማው የሚታይ

      ዓይኔ ከወደድሽ ከቶ ማን አለው ከልካይ
      አምነዋለሁ ልቤን አልሻም ሌላ አማካይ

      በሰዎች መሃል ሆነን እንኳ አለን የሚስጥር ዳርቻ፣

      (ማንም ሳያውቅብን ቃላትን ሳይወጣን
      በአንድ እይታ ብቻ ምንግባባው በጣም)

      ዓለም ልትመስል የግላችን የኔና ያንተ ብቻ

      (ፍቅራችን ሚስጥር ነው ቋንቋችን ላይገባው
      ልንዋደድ ሌላ ሰው በመሃል ላይገባ)

      ቃላት ሳናባክን ያግባባን ሃይል ነው ብርቱ

      (ከልቤ ተዋህደሽ በጥልቀት ገብተሻል
      ሆነሻል አስፈላጊ ላጣት የማልሻው)

      ልቤ ፈጠነ ምቱ አስተጋብቶብኝ ስሜቱ

      (ግራም ነፈሰ ቀኝ ሆነሻል የልቤ ዕጣ
      ፍቅርሽን አልሻም እንዳጣው)

      በይ እኮ

      ትቼህ እንዳልሄድ ሆኖ ስሜቴን መካድ
      እንዳልቆይ አብሬህ አጣሁት ያንተን ፈቃድ

      ስሜትህን ለመግለፅ ፍርሃትህ ካገደህ
      ካሳየኸኝ ፍቅር ድፍረትህ እየካደህ

      ልለይህ አልሻም ልቤ እየወደደህ፣ እየወደደህ

      Show more

      Playing Next