Playing Next....


      Jonny Ragga - Enas Min Alsh (Esat ) | ጆኒ ራጋ - እናስ ምን አልሽ (እሳት) New Ethiopian Music 2025



      ✔️ Click Here for More Musics

      Jonny Ragga - Enas Min Alsh (Esat )
      ጆኒ ራጋ - እናስ ምን አልሽ (እሳት)

      Track 5 of 7 from the album Jonny Ragga - Wiha Ena Esat | Esat

      Lyrics: Jonny Ragga
      Melody: Jonny Ragga
      Arrangement: Jonny Ragga
      Producer: Jonny Ragga

      Mixing: AYOMIPOSI Victor Oyewole at WarDrum Mixing Studio (UK)
      Mastering: Sonus (UK)

      © 2025 All Rights Reserved
      Produced by Jonny Ragga for Terara Music Production.
      Any unauthorized use, copying, or distribution is strictly prohibited.

      _______________________________________

      በሷ የመጣው 
      ለሁላችን ነው ጣጣው(Yeah)
      በርግጥ ፈተናዋ በርትቷል
      ብትወስን እሷም ልትገታው(Yeah)

      እኔም አንተም ሆነን በሷ ቦታ
      ቆመናል መከታ(Yeah)
      ይሄ ነው የሷ አማራጭ
      የለውም ሌላ አቋራጭ

      ይመስላል ድርጊትሽ ከማሰብ ቀና 
      ለሷ ካለሽ ምኞት ኑሮዋ እንዲቃና
      ከእህትሽ ጎን ቆመሽ ድምጿ እንዲሰማ
      መብቷንም ተምራ እንድትል ቀና

      ይመስላል ድርጊትሽ ከልብሽ ንቃት
      ምትሆኛት ጠበቃ ከሰነፍ ጥቃት
      የተባረከ ነው መሆንሽ ከለላ
      እሷን መታደግ ነው የሁሉም ስራ

      የራሷ ነው ያላት እሴት
      በፈጣሪ ቀመር ልኬት
      በአካል ልቦና ልዩ ናት ሴት
      የሚለያት ከወንድ አጥር
      የሴትነት ጥልቅ ሚስጥር

      የተላበሰች ልዩ ፍጡር
      ሴትነትን ከእናቷ፣ የተሻለ እስኪ የቷ
      አሳልፋ ሰጠች ራሷን ለቤቷ

      ገብቷት የህይወት ጥበብ፣ ሴትነት ላይሆን ሰበብ
      መሠረት የሆነች እናት የቤተሰብ
      እናስ ምን አልሽ፣ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ይኼ ነው የሚገባሽ ዝቅ አትበይ ከቦታሽ

      እናስ ምን አልሽ፣ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ትሆኛለሽ በስራሽ ከሁሉም የተሻልሽ
      እናስ ምን አልሽ፣ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ይኼ ነው የሚገባሽ ዝቅ አትበይ ከቦታሽ

      እናስ ምን አልሽ፣ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ትሆኛለሽ በስራሽ ከሁሉም የተሻልሽ
      የገበሬ ልጅ ናት ደርባባ
      ባህል ወግ ያላት ደርባ

      ያደገች ናት ቧጣ አፈር
      እንደወንድሞቿ ስራ የምትደፍር
      በገባችም ጊዜ ወደ ከተማ
      አንግባለች ብዙ አላማ

      እየተማረች ልትለፋ
      በከንቱ ጊዜ ላታጠፋ
      ልትጠብቅ የወላጆቿን አደራ
      በተክሊል ጋብቻ ህይወት ልትመራ
      ልጆችም ወልዳ ቤት ልታፈራ

      መች ቀሏት የከተሜው ኑሮ
      ያልጣላት ፅናቷ ጠንክሮ
      ገጥሟታል ፈተና ከሴቱም ከወንዱም
      ፈጽሞ አትፈቅድለት እንዲሰብሯት አንዱም

      ልብ ያላቸው ዕውነታ
      ክፋት የለውም ፆታ
      ያውቃል ገጥሟት በዓይኗም አይታ
      ሴት ለሴት ልጅ ጥቃት ሽፋን ሰጥታ

      ወንድና ሴት አይሆኑም እኩል 
      ይሄ አስኳላ በፍፁም ስንኩል
      በተለያየ ሚዛን የሚለኩ
      ልዩ ናቸው በተግባር መልኩ

      ቃላቱ ቢያምሩም አዝለዋል ተንኮል
      የተፈጥሮን ትእዛዝ የሚያደርግ ብኩን
      በስራቸው ይካሱ ይልቁን
      ደካማ እንርዳ አቅመቢስ እናግዝ እንዲሆን ብቁ

      ሆኖም በጾታ መገደብ ይቁም
      ህብረተሰብ አውቆ ቢነቃ
      እንዳይሰንፍ እህቱን ጥበቃ

      እሷም ወደ ላይ ጉዞ አታበቃ
      እስክትሆን ድረስ የወንድ የሴቱ የሁሉ አለቃ
      የራሷ ነው ያላት እሴት
      በፈጣሪ ቀመር ልኬት

      በአካል ልቦና ልዩ ናት ሴት
      የሚለያት ከወንድ አጥር
      የሴትነት ጥልቅ ሚስጥር

      የተላበሰች ልዩ ፍጡር
      ሴትነትን ከእናቷ፣ የተሻለ እስኪ የቷ
      አሳልፋ ሰጠች ራሷን ለቤቷ

      ገብቷት የህይወት ጥበብ፣ ሴትነት ላይሆን ሰበብ
      መሠረት የሆነች እናት የቤተሰብ

      እናስ ምን አልሽ፣ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ይኼ ነው የሚገባሽ ዝቅ አትበይ ከቦታሽ
      እናስ ምን አልሽ ልስማው ያንቺን ምላሽ
      ትሆኛለሽ በስራሽ ከሁሉም የተሻልሽ

      Show more

      Playing Next