Playing Next....


      HAILU AMERGA - AHUN (OFFICIAL MUSIC VIDEO)



      ✔️ Click Here for More Musics

      AHUN- Hailu Amerga
      Director: Kibralem Fanta Producer: Aklilu Gebremedhin Cinematography: Dagmawi Abebe Editor: Murree Ajeb Jarso Key Gaffer: Dagmawi Abebe AC: Kaleb Bedilu Production Manager: Beza Dawit Grip & Gaffer: Kaleb Bedilu Colorist: Murree Ajeb Jarso Runner: Yeabsira Agegnew

      Music Arrangement: Biruk Afeworq
      Melody: Hailu Amerga
      Lyrics: Aklilu Gebremedhin & Hailu Amerga
      Mixing & Mastering: Robel Dagne

      ርዕስ ፡ አሁን
      ዳይሬክተር ፡ ክብረዓለም ፋንታ : ፕሮዲዩሰር ፡ አክሊሉ ገብረመድህን : ሲኒማቶግራፊ ፡ ዳግማዊ አበበ : ኤዲተር ፡ መሪ አጀብ ጃርሶ : ረዳት ካሜራ ፡ ካሌብ በድሉ : ኪ ጋፈር ፡ ዳግማዊ አበበ : ከለር ፡ መሪ አጀብ ጃርሶ
      ፕሮዳክሽን ማናጀር ፡ ቤዛ ዳዊት : ራነር ፡ ያብስራ አገኘሁ : ግሪፕና ጋፈር ፡ ካሌብ በድሉ

      ቅንብር ፡ ብሩክ አፈወርቅ
      ዜማ ፡ ኃይሉ አመርጋ
      ግጥም ፡አክሊሉ ገብረመድህን ኃይሉ አመርጋ
      ሚክስና ማስተሪንግ ፡ ሮቤል ዳኜ

      ------------------------------------------------------------------------------------------------------
      አሁን
      አሁን አሁን
      አሁን አሁን
      በተሰጠኝ ልክ ልነሳ ልብረር
      የቀኑ ብርሃን ካይኔ እስኪሰወር
      ተፍ ተፍ ይላል እጅና እግሬ
      እስከማገኘው ደርሶ መልካሙን ፍሬ
      አዎ ዛሬ ላይ ነው
      ብርሃን የማየው
      ነገማ የሱ ድርሻ በፈቃዱ እስካየው
      አዎ ዛሬ ላይ ነው
      ብርሃን የማየው
      ነገማ የእሱ ድርሻ በፈቃዱ እስካየው
      ብድህም ብራመድ ብወድቅም አላፍር
      ተስፋን ሰንቂያለው ዛሬን የሚያሻግር
      አልተክዝም ብዝል አልባክን በዋዛ
      አሁን እተጋለው ደስታዬ እስኪበዛ
      አዎ ዛሬ ላይ ነው
      ብርሃን የማየው
      ነገማ የሱ ድርሻ በፈቃዱ እስካየው
      አዎ ዛሬ ላይ ነው
      ብርሃን የማየው
      ነገማ የእሱ ድርሻ በፈቃዱ እስካየው
      አሁን አሁን አሁን አሁን
      ዛሬን ተኝቼ ውዬ ትናንትን አልወቅስም
      በድሮ በሬ ትርክት ስንፍናን አልወርስም ስንፍና .....አልወርስም
      አልለቅ ብሎኝ የትናንት ፀፀት
      ይዞኝ ነበር ፍፁም የኋሊት
      ትካዜ አስሮኝ በእግር ብረት
      በመብከንከን ውስጥ ቀኔን በላሁት
      አሁን መንፈሴ ነቃ
      አሁን ልቤ ታደሰ
      አሁን ያሰረኝ ብረት
      አሁን ተበጣጠሰ
      አሁን ቀኔ ጀመረ
      አሁን እንደ አደይ ፈክቶ
      አሁን ባዘነው ፊቴ ሳቅ ተተክቶ
      አሁን ባዘነው ፊቴ ሳቅ ተተክቶ
      አሁን ባዘነው ፊቴ ሳቅ ተተክቶ ሃሃ
      ሃሃሃሃሃሃሃሃ
      ኣ.......አሁን ኣ ....አሁን ዬ.......ሄ ኤዬ ሄ

      #hailuamerga #Ethiopia #newmusicvideo #hailu #jano #hailujano #habesha #addisababa #sheger #ethiopianmusic #africa #africamusic #amba #newalbum #habesha #newalbum #ethiopiadiaspora #now #song #Ethipia

      Show more

      Playing Next